ثَمَٰنِيَةَ أَزْوَٰجٍ مِّنَ ٱلضَّأْنِ ٱثْنَيْنِ وَمِنَ ٱلْمَعْزِ ٱثْنَيْنِ قُلْ ءَآلذَّكَرَيْنِ حَرَّمَ أَمِ ٱلْأُنثَيَيْنِ أَمَّا ٱشْتَمَلَتْ عَلَيْهِ أَرْحَامُ ٱلْأُنثَيَيْنِ نَبِّـُٔونِى بِعِلْمٍ إِن كُنتُمْ صَٰدِقِينَ
Amharic Translation - Africa Academy143. ስምንትን ዓይነቶች፤ ከበግ ሁለትን (ወንድና ሴትን) ከፍየልም ሁለትን ፈጠረ:: «ከሁለቱም ክፍሎች አላህ ወንዶችን ብቻ እርም አደረገን? ወይንስ ሴቶችን ብቻ? ወይስ በእርሱ ላይ የሁለቱ ሴቶች ማህጸኖች ያጠቃለሉትን እርም አደረገ? እውነተኞች እንደሆናችሁ በእውቀት (በአስረጂ) ንገሩኝ» በላቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqስምንትን ዓይነቶች ከበግ ሁለትን (ወንድና ሴትን) ከፍየልም ሁለትን (ፈጠረ)፡፡«ከሁለቱም ክፍሎች አላህ ወንዶቹን እርም አደረገን ወይስ ሴቶቹን ወይስ በርሱ ላይ የሁለቱ ሴቶች ማሕፀኖች ያጠቃለሉትን እውነተኞች እንደሆናችሁ በዕውቀት (በአስረጅ) ንገሩኝ» በላቸው፡፡