قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَتَّخِذُ وَلِيًّا فَاطِرِ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَهُوَ يُطْعِمُ وَلَا يُطْعَمُ قُلْ إِنِّىٓ أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ
Amharic Translation - Africa Academy14. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከሆነው አላህ እርሱ ፍጡርን የሚመግብና ለራሱ የማይመገብ አምላክ ሲሆን ሌላን አምላክ እይዛለሁን?» በላቸው። «እኔ መጀመሪያ ትዕዛዝን ከተቀበለ ሰው እንድሆን ታዘዝኩ:: ‹ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትሁን።› ተብያለሁ።» በላቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ከኾነው አላህ እርሱ የሚመግብ የማይመገብ ሲኾን ሌላን አምላክ እይዛለሁን» በላቸው፡፡ «እኔ መጀመሪያ የሰለማ (ትእዛዝን ከተቀበለ) ሰው ልኾን ታዘዝኩ፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን (ተብያለሁ)» በላቸው፡፡