وَلَا تَسُبُّوا۟ ٱلَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ فَيَسُبُّوا۟ ٱللَّهَ عَدْوًۢا بِغَيْرِ عِلْمٍ كَذَٰلِكَ زَيَّنَّا لِكُلِّ أُمَّةٍ عَمَلَهُمْ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّهِم مَّرْجِعُهُمْ فَيُنَبِّئُهُم بِمَا كَانُوا۟ يَعْمَلُونَ
Amharic Translation - Africa Academy108. (ሙስሊሞች ሆይ!) እነዚያንም ከአላህ ሌላ የሚገዟቸውን ጣዖታትን አትስደቡ:: እነርሱም ድንበርን በማለፍ ያለ እውቀት አላህን ይሰድባሉና:: ልክ እንደዚሁ ለህዝቦች ሁሉ ስራቸውን ደግ አስመሰልንላቸው:: ከዚያም መመለሻቸው ወደ ጌታቸው ብቻ ነው:: ይሰሩት የነበሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእነዚያንም ከአላህ ሌላ የሚገዙዋቸውን (ጣዖታትን) አትስደቡ፡፡ ድንበርን በማለፍ ያለዕውቀት አላህን ይሰድባሉና፡፡ እንደዚሁ ለሕዝቦች ሁሉ ሥራቸውን ደግ አስመሰልንላቸው፡፡ ከዚያም መመለሻቸው ወደ ጌታቸው ነው፡፡ ይሠሩት የነበሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል፡፡