caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Mujaadila፣ አንቀጽ 22

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 105 · 58:22

لَّا تَجِدُ قَوْمًا يُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ يُوَآدُّونَ مَنْ حَآدَّ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَلَوْ كَانُوٓا۟ ءَابَآءَهُمْ أَوْ أَبْنَآءَهُمْ أَوْ إِخْوَٰنَهُمْ أَوْ عَشِيرَتَهُمْ أُو۟لَٰٓئِكَ كَتَبَ فِى قُلُوبِهِمُ ٱلْإِيمَٰنَ وَأَيَّدَهُم بِرُوحٍ مِّنْهُ وَيُدْخِلُهُمْ جَنَّٰتٍ تَجْرِى مِن تَحْتِهَا ٱلْأَنْهَٰرُ خَٰلِدِينَ فِيهَا رَضِىَ ٱللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا۟ عَنْهُ أُو۟لَٰٓئِكَ حِزْبُ ٱللَّهِ أَلَآ إِنَّ حِزْبَ ٱللَّهِ هُمُ ٱلْمُفْلِحُونَ

Amharic Translation - Africa Academy22. በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ህዝቦች አላህንና መልዕክተኛውን የሚከራከሩት ሰዎች አባቶቻቸው ወይም ልጆቻቸው ወይም ወንድሞቻቸው ወይም ዘመዶቻቸው ቢሆኑም እንኳ የሚወዳጁ ሆነው አታገኛቸዉም:: እነዚያ አላህ በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ጽፏል:: ከእርሱም በሆነ መንፈስ ደግፏቸዋል:: ከስሮቻቸዉም ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጣቸው ዘወታሪዎች ሲሆኑ ያስገባቸዋል:: አላህ ተግባራቸውን ወዷል:: እነርሱም የእርሱን ችሮታ ወደዋል:: እነዚያ የአላህ ህዝቦች ናቸው:: ንቁ! የአላህ ህዝቦች ምኞታቸውን የሚያገኙ እነርሱ ናቸው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ሕዝቦች አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩትን ሰዎች፤ አባቶቻቸው፣ ወይም ልጆቻቸው፣ ወይም ወንድሞቻቸው፣ ወይም ዘመዶቻቸው ቢኾኑም እንኳ የሚወዳጁ ኾነው አታገኛቸውም፡፡ እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ እምነትን ጽፏል፡፡ ከእርሱም በኾነ መንፈስ ደግፏቸዋል፡፡ ከሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ ያገባቸዋል፡፡ አላህ ከእነርሱ ወዷል፡፡ ከእርሱም ወደዋል፡፡ እነዚያ የአላህ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ንቁ! የአላህ ሕዝቦቸ እነርሱ ምኞታቸውን የሚያገኙ ናቸው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70