caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-Mujaadila፣ አንቀጽ 13

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 105 · 58:13

ءَأَشْفَقْتُمْ أَن تُقَدِّمُوا۟ بَيْنَ يَدَىْ نَجْوَىٰكُمْ صَدَقَٰتٍ فَإِذْ لَمْ تَفْعَلُوا۟ وَتَابَ ٱللَّهُ عَلَيْكُمْ فَأَقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُوا۟ ٱلزَّكَوٰةَ وَأَطِيعُوا۟ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَٱللَّهُ خَبِيرٌۢ بِمَا تَعْمَلُونَ

Amharic Translation - Africa Academy13. ከውይይታችሁ በፊት ምጽዋቶችን በማስቀደም ድህነትን ፈራችሁን? የታዘዛችሁትን ባልሰራችሁ ጊዜ አላህ ከናንተ ጸጸትን የተቀበለ ሲሆን ሶላትን ስገዱ፤ ዘካንም ስጡ፤ አላህንና መልዕክተኛውንም ታዘዙ:: አላህ በምትሰሩት ነገር ውስጠ አዋቂ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqከውይይታችሁ በፊት ምጽዋቶችን ከማስቀደም (ድህነትን) ፈራችሁን? ባልሠራችሁም ጊዜ አላህ ከእናንተ ጸጸትን የተቀበለ ሲኾን ሶላትን ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ አላህም ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70