يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِذَا قِيلَ لَكُمْ تَفَسَّحُوا۟ فِى ٱلْمَجَٰلِسِ فَٱفْسَحُوا۟ يَفْسَحِ ٱللَّهُ لَكُمْ وَإِذَا قِيلَ ٱنشُزُوا۟ فَٱنشُزُوا۟ يَرْفَعِ ٱللَّهُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنكُمْ وَٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْعِلْمَ دَرَجَٰتٍ وَٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرٌ
Amharic Translation - Africa Academy11. እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ በመቀመጫዎች ስፍራ ተስፋፉ በተባላችሁ ጊዜ ስፍራን አስፉ:: አላህ በገነት ያሰፋላችኃልና:: ተነሱ በተባለም ጊዜ ተነሱ:: አላህ ከናንተ መካከል እነዚያን በትክክል ያመኑትንና እነዚያንም እውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች (በዚች ዓለምም ሆነ በአኼራ) ከፍ ያደርጋል:: አላህ በምትሰሩት ነገር ሁሉ ውስጠ አወቂ ነውና::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለእናንተ በመቀመጫዎች ስፍራ ተስፋፉ በተባላችሁ ጊዜ (ስፍራን) አስፉ፡፡ አላህ ያሰፋላችኋልና፡፡ ተነሱ በተባላችሁም ጊዜ ተነሱ፡፡ አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እነዚያንም ዕውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል፡፡ አላህም በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡