مَّن كَانَ يُرِيدُ ٱلْعَاجِلَةَ عَجَّلْنَا لَهُۥ فِيهَا مَا نَشَآءُ لِمَن نُّرِيدُ ثُمَّ جَعَلْنَا لَهُۥ جَهَنَّمَ يَصْلَىٰهَا مَذْمُومًا مَّدْحُورًا
Amharic Translation - Africa Academy18. ጊዜያዊቱን ዓለም (በሥራው) የሚፈልግ ሁሉ ለእርሱ ከእርሷ ውስጥ የፈለግነውን ጸጋ ብቻ ለምንፈልገውም ብቻ እናስቸኩልለታለን:: ከዚያም ለእርሱ ገሀነምን መኖሪያ አድርገንለታል:: ተወቃሽና ከአላህ እዝነት የተባረረ ሆኖ ይገባባታል።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqቸኳይቱን ዓለም (በሥራው) የሚፈልግ ሰው ለእርሱ በርሷ ውስጥ የሻነውን (ጸጋ) ለምንሻው ሰው እናስቸኩልለታለን፡፡ ከዚያም ለእርሱ ገሀነምን (መኖሪያ) አድርገንለታል፡፡ ተወቃሽ ብራሪ ኾኖ ይገባታል፡፡