caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-An'aam፣ አንቀጽ 84

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 55 · 6:84

وَوَهَبْنَا لَهُۥٓ إِسْحَٰقَ وَيَعْقُوبَ كُلًّا هَدَيْنَا وَنُوحًا هَدَيْنَا مِن قَبْلُ وَمِن ذُرِّيَّتِهِۦ دَاوُۥدَ وَسُلَيْمَٰنَ وَأَيُّوبَ وَيُوسُفَ وَمُوسَىٰ وَهَٰرُونَ وَكَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلْمُحْسِنِينَ

Amharic Translation - Africa Academy84. ለእርሱም ልጁን ነብዩ ኢስሀቅንና የልጅ ልጁን ነብዩ የዕቆብን ሰጠነው:: ሁሉንም ወደ ቀናው መንገድ መራናቸው:: ኑህንም ከእነርሱ በፊት ወደ ቀናው መንገድ መራነው:: ከዘሮቹም ነብዩ ዳውድንም፤ ነብዩ ሱለይማንንም፤ ነብዩ አዩብንም፤ ነብዩ ዮሱፍንም፤ ነብዩ ሙሳንና፤ ነብዩ ሀሩንንም መራን:: በጎ ሰሪዎችን ሁሉ ልክ እንደዚሁ እንመነዳለን::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqለርሱም ኢስሐቅን (የልጅ ልጁን) ያዕቁብንም ሰጠነው፡፡ ሁሉንም መራን፡፡ ኑሕንም በፊት መራን፡፡ ከዘሮቹም ዳውድን፣ ሱለይማንንም፣ አዩብንም፣ ዩሱፍንም፣ ሙሳንም፣ ሃሩንንም (መራን)፡፡ እንደዚሁም በጎ ሰሪዎችን እንመነዳለን፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70