وَقَالُوا۟ لَوْلَآ أُنزِلَ عَلَيْهِ مَلَكٌ وَلَوْ أَنزَلْنَا مَلَكًا لَّقُضِىَ ٱلْأَمْرُ ثُمَّ لَا يُنظَرُونَ
Amharic Translation - Africa Academy8. «በእርሱ (በሙሐመድ) ላይ መልአክ ለምን አይወረድለትም?» አሉ። ነገር ግን መላዕክን ባወረድንለትና (ባያምኑ ኖሮ) የጥፋታቸው ነገር በተፈረደ ነበር:: ከዚያም አይቆዩም ነበር::
Amharic Translation - Muhammad Sadiq«በእርሱም (በሙሐመድ) ላይ መልአክ አይወረድለትም ኖሮአልን» አሉ፡፡ መልአክን ባወረድንም ኖሮ (ባያምኑ በጥፋታቸው) ነገሩ በተፈረደ ነበር፡፡ ከዚያም አይቆዩም ነበር፡፡