caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ Al-An'aam፣ አንቀጽ 73

መካ · የወረደበት ቅደም ተከተል 55 · 6:73

وَهُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ بِٱلْحَقِّ وَيَوْمَ يَقُولُ كُن فَيَكُونُ قَوْلُهُ ٱلْحَقُّ وَلَهُ ٱلْمُلْكُ يَوْمَ يُنفَخُ فِى ٱلصُّورِ عَٰلِمُ ٱلْغَيْبِ وَٱلشَّهَٰدَةِ وَهُوَ ٱلْحَكِيمُ ٱلْخَبِيرُ

Amharic Translation - Africa Academy73. እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በትክክል የፈጠረ ነው:: (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «ሁን» የሚልበትንና ወዲያዉም የሚሆንበትን ቀን አስታውስ:: ቃሉም እውነት ነው:: በቀንዱ በሚነፋበት ቀንም ንግስናው የእርሱ ብቻ ነው:: ሩቁንና ቅርቡን አዋቂ ነው:: እርሱም ጥበበኛውና ውስጠ አዋቂው ነው::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqእርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በእውነት የፈጠረ ነው፡፡ «ኹን» የሚልበትንና ወዲያውም የሚኾንበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ ቃሉ እውነት ነው፡፡ በቀንዱም በሚነፋ ቀን ንግሥናው የርሱ ብቻ ነው፡፡ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ጥበበኛው ውስጥ ዐዋቂው ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70