قُلْ أَغَيْرَ ٱللَّهِ أَبْغِى رَبًّا وَهُوَ رَبُّ كُلِّ شَىْءٍ وَلَا تَكْسِبُ كُلُّ نَفْسٍ إِلَّا عَلَيْهَا وَلَا تَزِرُ وَازِرَةٌ وِزْرَ أُخْرَىٰ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُم مَّرْجِعُكُمْ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ فِيهِ تَخْتَلِفُونَ
Amharic Translation - Africa Academy164. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) «አላህ የሁሉ ጌታ ሲሆን ከአላህ በስተቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን? ነፍስ ሁሉ በራሷ ላይ እንጂ ክፉን አትሰራም:: ወንጀለኛ ነፍስ ሁሉ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢአት አትሸከምም:: ከዚያ መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ነው:: ከዚያም ትለያዩበት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል» በላቸው።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqበላቸው «እርሱ (አላህ) የሁሉ ጌታ ሲኾን ከአላህ በቀር ሌላን ጌታ እፈልጋለሁን? ነፍስም ሁሉ በራሷ ላይ እንጅ (ክፉን) አትሠራም፡፡ ተሸካሚም (ነፍስ) የሌላይቱን ሸክም (ኃጢአት) አትሸከምም፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ነው፡፡ ወዲያውም በእርሱ ትለያዩበት የነበራችሁትን ሁሉ ይነገራችኋል፡፡»