أَلَمْ تَرَ أَنَّ ٱللَّهَ يُزْجِى سَحَابًا ثُمَّ يُؤَلِّفُ بَيْنَهُۥ ثُمَّ يَجْعَلُهُۥ رُكَامًا فَتَرَى ٱلْوَدْقَ يَخْرُجُ مِنْ خِلَٰلِهِۦ وَيُنَزِّلُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مِن جِبَالٍ فِيهَا مِنۢ بَرَدٍ فَيُصِيبُ بِهِۦ مَن يَشَآءُ وَيَصْرِفُهُۥ عَن مَّن يَشَآءُ يَكَادُ سَنَا بَرْقِهِۦ يَذْهَبُ بِٱلْأَبْصَٰرِ
Amharic Translation - Africa Academy43. (መልዕክተኛችን ሙሐመድ ሆይ!) አላህ ደመናን የሚነዳ መሆኑን አላየህምን? ከዚያም ከፊሉን ከከፊሉ ያገናኛል፤ ከዚያም የተደራረበ ያደርገዋል፤ ዝናቡንም ከመካከሉ የሚወጣ ሆኖ ታየዋለህ፤ ከሰማይም ከደመናም በውስጡ ካሉት ጋራዎችም በረዶን ያወርዳል:: በእርሱም የሚሻውን ሰው በጉዳት ይነካል:: ከሻዉም ሰው ላይ ይመልሰዋል:: የብልጭታው ብርሃን ዓይኖችን ሊወስድ ይቀርባል::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ ደመናን የሚነዳ መኾኑን አላየህምን? ከዚያም ከፊሉን ከከፊሉ ያገናኛል፡፡ ከዚያም የተደራረበ ያደርገዋል፡፡ ዝናቡንም ከመካከሉ የሚወጣ ኾኖ ታየዋለህ፡፡ ከሰማይም (ከደመና) በውስጧ ካሉት ጋራዎች በረዶን ያወርዳል፡፡ በእርሱም የሚሻውን ሰው (በጉዳት) ይነካል፡፡ ከሚሻውም ሰው ላይ ይመልሰዋል፡፡ የብልጭታው ብርሃን ዓይኖችን ሊወስድ ይቀርባል፡፡