caseriqበቁርኣን ውስጥ የትርጉም ፍለጋ

ሱረቱ An-Noor፣ አንቀጽ 35

መዲና · የወረደበት ቅደም ተከተል 102 · 24:35

ٱللَّهُ نُورُ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ مَثَلُ نُورِهِۦ كَمِشْكَوٰةٍ فِيهَا مِصْبَاحٌ ٱلْمِصْبَاحُ فِى زُجَاجَةٍ ٱلزُّجَاجَةُ كَأَنَّهَا كَوْكَبٌ دُرِّىٌّ يُوقَدُ مِن شَجَرَةٍ مُّبَٰرَكَةٍ زَيْتُونَةٍ لَّا شَرْقِيَّةٍ وَلَا غَرْبِيَّةٍ يَكَادُ زَيْتُهَا يُضِىٓءُ وَلَوْ لَمْ تَمْسَسْهُ نَارٌ نُّورٌ عَلَىٰ نُورٍ يَهْدِى ٱللَّهُ لِنُورِهِۦ مَن يَشَآءُ وَيَضْرِبُ ٱللَّهُ ٱلْأَمْثَٰلَ لِلنَّاسِ وَٱللَّهُ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌ

Amharic Translation - Africa Academy35. አላህ የሰማያትና የምድር ብርሃን (አብሪ) ነው፤ የብርሃኑ ምሳሌ በውስጡ መብራት እንዳለባት ዝግ መስኮት፤ መብራቱ በብርጭቆ ውስጥ የሆነ፤ ብርጭቆው ደግሞ ፍጹም ሉላዊ ክብ የምትመስል ምስራቃዊም ምዕራባዊም ካልሆነች፤ ከተባረከች የወይራ ዛፍ ዘይቷ እሳት ባይነካዉም እንኳ ሊያበራ የሚቀርብ ከሆነች ዘይት የሚቃጠል እንደሆነ መብራት ነው:: ይህ በብርሃን ላይ የሆነ ብርሃን ነው:: አላህ ወደ ብርሃኑ የሚሻውን ሰው ይመራል:: አላህም ለሰዎች ምሳሌዎችን ያቀርባል። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ ነውና።
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህ የሰማያትና የምድር ብርሃን (አብሪ) ነው፡፡ የብርሃኑ ምሳሌ በውስጧ መብራት እንዳለባት (ዝግ) መስኮት፣ መብራቱ በብርጭቆ ውስጥ የኾነ፣ ብርጭቆይቱ ፍፁም ሉላዊ ኮከብ የምትመሰል ምሥራቃዊው ምዕራባዊም ካልኾነች፤ ከተባረከች የወይራ ዛፍ ዘይቷ እሳት ባይነካውም እንኳ ሊያበራ የሚቀርብ ከኾነች (ዘይት) የሚቃጠል እንደ ሆነ (መብራት) ነው፡፡ (ይህ) በብርሃን ላይ የኾነ ብርሃን ነው፡፡ አላህ ወደ ብርሃኑ የሚሻውን ሰው ይመራል፡፡ አላህም ለሰዎች ምሳሌዎችን ያቀርባል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
ርዕስ እየፈለጉ ነው? የትርጉም ፍለጋን ይሞክሩ — ጥያቄዎ በ6,236 አንቀጾች ውስጥ ይፈለጋል።
ቋንቋ — 70