وَإِذْ يَعِدُكُمُ ٱللَّهُ إِحْدَى ٱلطَّآئِفَتَيْنِ أَنَّهَا لَكُمْ وَتَوَدُّونَ أَنَّ غَيْرَ ذَاتِ ٱلشَّوْكَةِ تَكُونُ لَكُمْ وَيُرِيدُ ٱللَّهُ أَن يُحِقَّ ٱلْحَقَّ بِكَلِمَٰتِهِۦ وَيَقْطَعَ دَابِرَ ٱلْكَٰفِرِينَ
Amharic Translation - Africa Academy7. (እናንተ ተከራካሪዎች ሆይ!)፤ አላህ ከሁለቱ ቡድኖች አንደኛዋን ለእናንተ ናት ሲል ተስፋ በሰጣችሁና የኃይል ባለቤት ያልሆነችውን የነጋዴይቱን ቡድን ለእናንተ ልትሆን በወደዳችሁ ጊዜ አላህም በተስፋ ቃላቱ እውነቱን ማረጋገጡን ሊገልጽና የካሓዲያንንም መጨረሻ ሊቆርጥ በፈለገ ጊዜ (የሆነውን አስታውስ)::
Amharic Translation - Muhammad Sadiqአላህም ከሁለቱ ጭፍሮች አንደኛዋን እርሷ ለናንተ ናት ሲል ተስፋ በሰጣችሁ ጊዜ፣ የሀይል ባለቤት ያልኾነችውም (ነጋዴይቱ) ለናንተ ልትኾን በወደዳችሁ ጊዜ፣ አላህም በተስፋ ቃላቱ እውነትን ማረጋገጡን ሊገልጽና የከሓዲዎችንም መጨረሻ ሊቆርጥ በሻ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡